ሰኞ 29 ዲሴምበር 2014

በጎ ሕሊና ይኑርህ


የደብራችን አገልጋይ የነበረው ዲያቆን ተሾመ አበራ ካለበት የቲኦሎጂ ት/ም ቤት በጎ ህሊና በሚል ርዕስ በኢሜል የላከልንን ጽሁፍ አቅርበንላችኋል፤ ለወንድማችን ቃለ ህይወት ያሰማልን ! ‪#‎TeshomeAbera‬
በጎ ሕሊና ይኑርህ 1ጢሞ 1፡19
በዲያቆን ተሾመ አበራ የአምስተኛ አመት የቲዖሎጂ ደቀመዝሙር
በጎ ሕሊና ይኑርህ 1ጢሞ 1፡19
የዚህች አናሳ ጽሁፍ አላማ ሁሉም ክርስቲያን በጎ የሆነ ሕሊና ሊኖረዉ እንደሚገባ ለማስጨበጥ ነዉ ፡፡
ቃሉን የተናገረዉ ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳዉሎስ ሲሆን ቃሉን የጻፈለትም ለግዜዉ ለመንፍስ ልጁ ለጢሞቲዎስ ነዉ፡፡ በመጨረሻም ለኛ ለክርስቲያኖች ተጽፎልናል፡፡
በመጀመርያ ሕሊና ምንድነዉ ?ሕሊና በመልካም እና በክፉ መካከል የሚለይ በጥፋቱ ሰዉን የሚከስ ነዉ፡፡ ሕሊና ማለት ስለ ክፉም ሆነ ስለ መልካም ሥራዉ ሰዉን እንዲያመዛዝን የሚያሳስብ ነዉ፡፡ሕሊና የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ ነዉ፡፡ሕሊና እግዚአብሔር በስዉ ልጅ ዉስጥ የተከለለት የግብረ ገብነት(ሞራል) ምስክር ነዉ፡፡አንድ ክርስቲያን በጎሕሊና አለዉ የሚባለዉ መልካምን ሁሉ ሲያደርግ እና መጥፎ የተባሉትን ነገሮች ማስወገድ ሲችል ነዉ(ዮሐ23፡1)፡፡ ውድ ክርስቲያኖች ሕሊና የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ ስለሆነ በአግባቡ ብንጠቀምበት በሕይወታችን ዉስጥ የሚገኘዉን ማንኛዉንም ጥቁር ነጥብ ነጥሎ እንዲያወጣልን ግዜ ሳያልፍ እና ለክፉ ተላልፈን ሳንሰጥ እንድንጠነቀቅ ይረዳናል፡፡ውድ ዘመዶቼ የእግዚአብሔርን መንፍስ የሕሊናችን አጋር እንዲሆን ከመፍቀድ የመሰለ አስተማማኝ ሁኔታ የለም ፡፡ይህ እንዲሆን ግን ራስን ማዘጋጀት እና ከእዉነት ጋር ለመተባበር የወሰነ ማንነት ሊኖረን ይገባል፡፡ሕሊናችንን ብናሰለጥነዉ እና ለሚሰጠም ምልክት ትኩረት ብንሰጠዉ ከብዙ ጸጸት ፣እረፍት ማጣት፤ሰላም ማጣት እና ስቃይ እንድናለን፡፡ እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች በጎ ሕሊና ይኑርህ በማለት ሐዋርያዉ ለመንፍስ ልጁ ለጢሞቲዎስ ይምክረዋል ለእኛም እንደዚሁ ያስተምረናል፡፡ ምክንቱም በጎ ሕሊና ለክርስቲያኖች ወሳኝ ስለሆነ ነዉ፡፡ በጎ ሕሊና ያለዉ ክርስቲያን የሰዉን ስሜት አይጎዳም፤ ከበጎ ምግባር ጋር ሁሉ ይተባበራል፤ በጎ ነገርን እንደ ዉሃ ይጠማል፤ ሕይወቱ በአጠቃላይ በበጎ ምግባር ያሸበረቀ ይሆናል፤ ነገሮችን በትክክል ያመዛዝናል ፤ለሰዉ ልጆች ሁሉ ተገቢዉን ክብር አይነፍግም፤ ምንም እንኩዋን ከማይጠፋ ዘር ቢወለድም በስጋዉ እንደ ጤዛ ረጋፊ መሆኑን ያስተዉላል፡፡እንደ መጽሓፍ ቅዱስ ሀሳብ ሶስት ዐይነት ሕሊና አሉ፡፡

 
 1. በጎሕሊና ፤ከፉዉን ከደጉ የለየና ኃጥያት ሲሰራ የሚወቅስ ነዉ፡፡በጎ ሕሊና ያለዉ ሰዉ ስህተት ሰርቶ እንዳልሰራ ማለፍ አይችልም የልቁንም ይወቅሳል ፤ይመክራል እንጂ፡፡ እንዲህ አይነት ህሊና ያለዉ ክርስቲያን ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰዉ ጋር የሰመረ ግንኙነት አለዉ(1ጢሞ 1፡5)፡፡
2. ደካማ ሕሊና፤ ደካማ ሕሊና ያለዉ ሰዉ በየምክንያቱ እራሱን የሚወቅስ ሰዉ ነዉ፡፡ ባጠፋዉም ሆነ ባላጠፋዉ ነገር የሚጸጸት እና የጥፋኝነት ስሜት የሚያጠቃዉ ሰዉ ነዉ፡፡እንዲህ አይነቱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል በመሞላት እና በመብሰል ማደግ ይኖርበታል (1ቆሮ8፡7)፡፡
3. ክፉ ሕሊና ፡የተበላሸ እና ሐጥያት ሆነ ክፋት ሲሰራ ከመወቀስ ዉጭ የሆነ ሕሊና ነዉ፡፡ይህ አይነት ሕሊና ያለዉ ሰዉ ምንም ነገር ለማድረግ የማይከለከል ነዉ፡፡ሕሊናዉን ሕይወት አልባ እንዲሆን ስላደረገዉ አይወቅሰዉም (ዕበ 10፡22)፡፡
ታድያ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች የእኛ ሕሊና ከየትኛዉ ወገን ይሆን ? ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳዉሎስ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ በማለት ያስተምረናል ስለዚህ በጎ ሕሊና ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡በጎንም ነገር ለመስራት ልንትጋ ይገባል፤ለዚህ ነዉ ቅዱስ ጴጥሮስ በጎንምለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነዉ ? በማለት ያስተማረን (1ጴጥ 3፡13)፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር በጎ የሆነውን እንድናስብ፤በጎ የሆነውንም ተግባር እንድንሰራ በቸርነቱ ያግዘን፡፡

ወስብሓት ለእግዚአብሔር
አዘጋጅ:- ዲያቆን ተሾመ አበራ የአምስተኛ አመት ቲዖሎጂ ደቀመዝሙር

ዓርብ 5 ዲሴምበር 2014

ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው ለሚለው ኑፋቄ የተሰጠ ምላሽ



Sewaferawe Alene

ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ይህንን ቃል ደጋግመው ሲያነሱ እና እውነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስመስለው ፌስ ቡክ ላይ ሲለቁት ተመልክታችሁ ይሆናል፡፡ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለመቃወም እና ምእመኑን ከእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ለማውጣት እና ለዲያብሎስ ለማስረከብ በማሰብ ነው፡፡ቤተክርስቲያናችን ዘወትር እግዚአብሔርን በልቧ በተግባርና በአምልኮ ስርአቷ ትቀድሰዋለች /ታመሰግነዋለች/፡፡ቅዳሴ ማለት ምስጋና ማለት ነው ፡፡መናፍቃን ግን ለመተቸት ‹‹ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው››እያሉ ሲፎክሩና ሲሸልሉ በሀይማኖት ያልበሰሉትንም ሲያደናግሩ እንመለከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዳሴ/ጌታን ስለመቀደስ ምን ይላል እስቲ እንመልከተው፡፡
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
3፥15
ሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
8፥13
ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
የማቴዎስ ወንጌል
6፥10
ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ኦሪት ዘኍልቍ
20፥12
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል
11፥2
አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ታዲያ ቤተክርስቲያን ምን አጠፋች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባገኘችው ቃል ነው ቅዳሴ የምትቀድሰው/ጌታን የምታመሰግነው/
ለምትሰጡኝ አስተያየት መጽሀፍ ቅዱስ እንጂ ትችት እንዳይሆን
ጌታ ለመናፍቃኑ ልቦና ይስጣቸው

ዓርብ 28 ኖቬምበር 2014

Bible say about racism

"What does the Bible say about racism, prejudice, and discrimination?"
ስለ የሰው ዘር ወይም ዘረኝነት መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይላል/Amharic Ethiopian Language


“There is neither Jew nor Greek, slave nor free, male nor female, for you are all one in Christ Jesus.”
                                                                                                                                        Galatians 3:28
The first thing to understand in this discussion is that there is only one race—the human race. Caucasians, Africans, Asians, Indians, Arabs, and Jews are not different races. Rather, they are different ethnicities of the human race. All human beings have the same physical characteristics (with minor variations, of course). More importantly, all human beings are created in the image and likeness of God (Genesis 1:26-27). God loved the world so much that He sent Jesus to lay down His life for us (John 3:16). The “world” obviously includes all ethnic groups.

God does not show partiality or favoritism (Deuteronomy 10:17; Acts 10:34; Romans 2:11; Ephesians 6:9), and neither should we. James 2:4 describes those who discriminate as “judges with evil thoughts.” Instead, we are to love our neighbors as ourselves (James 2:8). In the Old Testament, God divided humanity into two “racial” groups: Jews and Gentiles. God’s intent was for the Jews to be a kingdom of priests, ministering to the Gentile nations. Instead, for the most part, the Jews became proud of their status and despised the Gentiles. Jesus Christ put an end to this, destroying the dividing wall of hostility (Ephesians 2:14). All forms of racism, prejudice, and discrimination are affronts to the work of Christ on the cross.

Jesus commands us to love one another as He loves us (John 13:34). If God is impartial and loves us with impartiality, then we need to love others with that same high standard. Jesus teaches in Matthew 25 that whatever we do to the least of His brothers, we do to Him. If we treat a person with contempt, we are mistreating a person created in God’s image; we are hurting somebody whom God loves and for whom Jesus died.

Racism, in varying forms and to various degrees, has been a plague on humanity for thousands of years. Brothers and sisters of all ethnicities, this should not be. Victims of racism, prejudice, and discrimination need to forgive. Ephesians 4:32 declares, “Be kind and compassionate to one another, forgiving each other, just as in Christ God forgave you.” Racists may not deserve your forgiveness, but we deserved God’s forgiveness far less. Those who practice racism, prejudice, and discrimination need to repent. “Present yourselves to God as being alive from the dead, and your members as instruments of righteousness to God” (Romans 6:13). May Galatians 3:28 be completely realized, “There is neither Jew nor Greek, slave nor free, male nor female, for you are all one in Christ Jesus.”

ሰኞ 24 ኖቬምበር 2014

ጾመ ነብያት(የገና ጾም

“ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥”

ጾም በብሉይ ኪዳን
ት.ዳን 10፤2
“በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም”።
ት.ኢዩ 2፤15
“ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥”
መዝ.108 (109) ፤24
“ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ”።
ኢያ.7፤6-9 ፤አስ 4፤16፤2ኛ ሳሙ.12፤17፤ዘዳ 9፤9-18፤ ዘዳ10፤10፤1ኛ ነገ.19፤6-10፤
ጾም በሀዲስ ኪዳን
ማር 9፤29
“ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው”።
ማቴ.6፤16
“ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል”።
ሉቃ. 6፤21
“እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና”።
የሐዋ.ሥራ 13፤3
“በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው”።
በዚህ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት በቤተ ክርስቲያናችን በአዋጅ የሚጾሙ ሰባት አጽዋማት አሉ፤
እነዚህም፡- 1.አብይ ጾም 2.ጾመ ሐዋርያት 3. ጾመ ነብያት(የገና ጾም) 4. ጾመ ፍልሰታ 5.ጾመ ድኅነት(አርብና ረቡዕ) 6.ጾመ ነነዌ 7.ጾመ ገሀድ(በጥምቀት ጥር 10 ቀን የሚጾም) ሲሆኑ ፡-
ከነዚህ መካከል የነብያት ጾም ጾመ ስብከትም ይባላል አበው ነብያት በትንቢት የክርስቶስን መምጣት ከመስበክ ባለፈ አምነው የሰበኩት ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ በጾምና በጸሎት ይማጸኑ ነበር ቃሉን የማይጥፈው እግዚአብሔር አምላክም አንድያ ልጁን ልኮ ዓለምን በልጁ በክርስቶስ በደሙ ዋጅቷል፡፡ አሁን እኛም ምዕመናን የአበውን ፈለግ በመከተል ይህንን ጾም እንጾማለን ፡፡ የ2007 ዓ/ም ጾመ ነብያት ከህዳር 15-29 ይጾማል ፤እግዚአብሔር ከጾሙ በረከት ያሳትፈን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ዓርብ 7 ኖቬምበር 2014

‹‹ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ተመልከቱ ››


መልዕክት ለወጣቶችና ለወላጆች !
በስመ አብ ወወለድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ሰንበት በትምህርት ቤቶች በየአጥቢያው ሲመሠረቱ ሊታደጓቸው ከወጠኑት የምዕመናን ክፍል ዋነኞቹ ህጻናትና ወጣቶች መሆናቸው ይታወቃል ፤ብዙ ወጣቶችና ህጻናት በመልካም ስነ-ምግባር መታነጽ የቻሉ ሲሆን አሁንም በዚሁ ሂደት ብዙ ወጣቶቸ በመታነጽ ላይ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን በተለያዩ ወቅቶች የተነሱ መናፍቃንና አላውያን ምዕመናንን በተለይ ወጣቶችን እግዚአብሔርን ከሚያመልኩበት ከዕውነተኛው ዕምነታቸው ከተዋህዶ ለመንጠቅ የተለያዩ ባህሪያትን እየተላበሱና ባህሪያቸውን እየቀያየሩ እስከ ቤ/ክ ቅጽር ድረስ ዘልቀው በመግባት በተለይ በወጣቶች ሰ/ት/ቤት ጨዋ መስለውና የበግ ለምድ ለብሰው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እጅግ በረቀቀ መንገድ እያራመዱ ጥቂት የማይባሉ ወጣቶችን ማስኮብለል ቢችሉም ኋላ ግን በተለያዩ ግዜያት አንዳንዶች ተደርሶባቸው ሌሎች ግብራቸው እየገለጣቸው ከኛ ወገን አልነበሩምና ከኛ ዘንድ ወጡ ከኛ ወገን ቢሆኑስ ቅዱስ ዮሐንስ እንደተናገረው ከኛ ጋር ጸንተው በቆዩ ነበር ፤1ኛ ዮሐ.2፤19

ምዕመናንን ለማስኮብለል ከሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የማስኮበለያ ሰልቶች አንዱ ከዚህ በፊት በስፋት ሲጠቀሙበት የኖሩትን ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ጥቅሶችን በመምዝ ለማደናገሪያነት በመጠቀም በእምነት የደከሙትን የመንጠቅ ሥራ ተወት በማድረግ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚታዩ የአስተዳደር ክፍተቶችን እንደመነሻ በመጠቀም በቀጣይ ሌሎች ኑፋቄዎችን በማንሳት ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠሉ በማድረግ ለማሰኮብለል ጥረት ሲያረደርጉ ቆይተዋል አሁንም ከዚህ ሥራቸው አልተቆጠቡም፤ ይህንን እኩይ ተግባራቸውን ከኛ ወገን የሆኑና በሴራቸው ሳያውቁ የተጠለፉ ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤታችን ደረጃ ግለሰቦቹን ለይተን ከማወቅ በተጫማሪ የተለያዩ የአባቶችንና የወንድሞችን ምክር እንዲያገኙ ተደርገው ከተገባራቸው የታቀቡና የዕውቀት ክፍተቶቻቸውን እያሻሻሉ የመጡ ብዙ ወጣቶች ቢኖሩም አሁንም ድረስ በንቀትና ከኔ በላይ አዋቂ በሚል መታበይ ከነኑፋቄያቸው የሚመላለሱ እንዳሉ ሁሉ እንደ ወትሮው ወደ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ወጣቶችን መንጠቅ ሲሳናቸው በየጎዳናው ፤በትምህርት ቤት ፤በመዝናኛ ስፍራዎች የሚገኙ ወጣቶችን በኑፋቄያቸው በማጥመድ ላይ ይገኛሉ በዚህ ሂደትም ቀላል የማይባሉ የከተማችን ወጣቶች በነዚህ የአምልኮ መልክ ባላቸው ኃይሉን ግን በካዱ አላውያን እየተወሰዱ ይገኛሉ ፤
ሆኖም ግን ለዚህ ሥራቸው አመቺ ከሆኑ ነገሮች መካከል፡-
1ኛ- ወጣቶች ቤተ ክርስቲያን ቀርቦ የእግዚአብሔርን ቃል ከመማር ይልቅ ለስጋቸው በማድላት በመዝናኛ ስፍራ ብቻ ማሳለፍና በሰንበት በሳምንት አንድ ቀን እንኳ ቤ/ክ መምጣት አለመቻላቸው ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን የት አግኝታ ማስተማር እንደምትችል ግራ የሚያጋባ መሆኑ፤
2ኛ-ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ቤተ-ክርስቲያን የማይልኩ ከመሆናቸው ባሻገር የት እንደሚውሉ እንኳን የማይከታተሉ መሆኑ፤
3ኛ- ለመማር የቀረቡ ወጣቶችም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከሥር መሠረቱ አጠናቆና ታግሶ ከመማርና ራሳቸውንም ቅዱሳን መጻህፍትን በማንበብ ዕውቀታቸውን በማጎልበት ህይወት የሚያገኙበትን ቃለ-እግዚአብሔርን ከማወቅ በተጨማሪ ለሚጠይቋቸው መልስ ለመስጠት ከመዘጋጀት/1ኛጴጥ.3፤15/ መስነፍና የማውቀው ይበቃኛል ማለት ፤ የተሻለ ዕውቀት ያላቸውም ቢሆኑ መክሊታቸውን ከማትረፍ መዘግየታቸው ዋና ዋና ችግሮች ናቸው፡፡
በመሆኑም ወላጆች ልጆቻችሁን ለማሳደግ መክፈል ከሚገባችሁ ወጪ ከማይጠይቀው ኃላፊነትና ውለታችሁ አንዱ ልጆቻችሁን ወደ ቤተ እግዚአብሔር መላክ አንዱና ዋነኛው ነው ይህን ሳታደርጉ ቀርታችሁ ልጆቻችሁ በስነ-ምግባር ችግሮች ቢተበተቡ፤ በአሳሳቾች መናፍቃን ተነጥቀው ከመጸጸት ይልቅ ከወዲሁ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡
ወጣቶች ሆይ ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፤
‹‹ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም››1ኛ ቆሮ.1፤26-28 ይላል በመሆኑም ለስጋ ከማድላት ይልቅ ለነፍስ ማድላት መልካም ነውና በተለይ አንዳንድ ወጣቶች ከአጓጉል ሱሳሱስ፤ ከዘፈንና ከጭፈራ በመራቅ ባዕላትን ጠብቆ ብቅ ከማለት ተቆጥባችሁ ለነፍሳችሁ ዋጋ በመስጠት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመቅረብ ቃለ-እግዚአብሔርን ትመገቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ሥም እንለምናችኋለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የአ/ነ/ደ/ል/ቅ/ጊ/ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት

ቅዳሜ 23 ኦገስት 2014

እንኳን አደረሳችሁ !


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ይህ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሞት የመነሳት ምስጢር ለበዙዎች አልዋጥላችሁ ብሏቸዋል፡፡ እንደውም ይህን ስንናገር አምላክ ያደረግናት ይመስላቸዋል፡፡ሌሎች ደግሞ እሷን ከጌታችን ጋር እኩል ለማድረግ እየጣርን ያለንና የፈጠራ ወሬ እያወራን ለማሳመን የምንሞክር ይመስላቸዋል ይህ ሁሉ ግን በዕርግጥ ትክክለኛ አስተሳሰብ እይደልም፡፡መጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሞትን እንኳ ያልቀመሱ እስከ አሁን እንዳሉ ይነገራል፡፡ ለምሳሌ ያህል ሄኖክ አልሞተም፡፡ “ሄኖክም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና”፡፡ ዘፍ.5፤27 ከእግዚአብሔር ጋር አካሔዱን በማድረጉ ከተወሰደው ሔኖክ ይልቅ በእግዚአብሔር ጸጋ የተሰጣት መንፈስ ቅዱስ የጸለለባት አምላካችንን የወለደች እመቤታችን ተነስታለች አርጋለች ቢባል ምን ይገርማል ኢያሱ ከአሞራውያን ጋር በተዋጋ ጊዜ ጸሀይ እንዳትጠልቅ በማድረግ አቁሟታል፤ እያሱ.10፤12 ይህ በማን ሆነ እንዴት ሆነ ብለን ልንቃወመው አንችልም ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ማድረግ እንደሚችል ብቻ እናውቃለን፤ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሀዋርያትን ሲያስተምር እውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ በመንግስቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ከዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱት እንዳንዶች አሉ ማቴ 16፤26 ኤልያስ በደመና ተነጥቋል፤2ኛ ነገ. 2፤11 ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “የሚያምንብኝ ቢኖር እኔ የማደርገውን ብቻ ሳይሆን ከእኔም የበለጠ ያደርጋል” ዮሐ 14፤12 ብሏል ይልቅ የአምላክ እናት ከሁሉ የተለየሽ የተባለችና ከነብያትና ከሐዋርያት ትበልጫለሽ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ ዘንድ ማረጓ ለአንዳንዶች ለምን አይዋጥላቸውም እንዴትስ በዚህ ነገር ይሰናከላሉ?
የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን /መግነዟን/ ሰጥታዋለች ሐዋርያው ቶማስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይሆናል?” ቢላቸው፡፡ “የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም ለምን አታምንምን;” ብለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ይዘውት ሄደው መቃብሩን ቢከፍቱ ሥጋዋን አጡት፡፡ ደነገጡም፡፡ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችን ተነሥታ ዐርጋለች” ብሎየሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡ ለማረጋገጫ ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ሰበኗን /መግነዟን/ ለበረከት ቆራርጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደ የአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡ሐዋርያትም “እርሱ (ቶማስ) ትንሣኤሽንና ዕርገትሽን አይቶ እኛ ለዚህ ዕድል ሳንበቃ እንዴት እንቀራለን?” በማለት አዝነው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በመጨረሻም ነሐሴ 16 ቀን ጌታችን ጸሎታቸውን ተቀብሎ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን መንበር፣ ራሱን ሠራዒ ቄስ፣ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ረዳት ካህን፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ (ዋና) ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ ዕርገቷን ለማየት አብቅቶአቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ከእመቤታችን ትንሳዔ በረከት ያሳትፈን ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡

ሰኞ 18 ኦገስት 2014

ደብረ ታቦር


እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
ደብረ ታቦር

ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው ፡፡በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤የደመቀ የጎላ ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው ፡፡የችቦ ማብራት ቱፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው ፡፡
ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ተራራው ከገሊላ ባህር በስተ ምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል፤መሳ4፤6-14
ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤
ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ሌሎች ኤልያስ ነው፤ ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ ነው ይላሉ ብለውት ነበር፤ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ’’ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስደስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል 3ቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርሀን አሳየኝ ብሎት ነበር ዘጸ (33፤17-23) ጌታችን ግን በሕይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል ፡፡
ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለአለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል፡፡ ከዚያም ዳመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ የምወደው ልጄ እርሱ ነው አርሱን ስሙት ሲል መሰከረ፡፡ማቴ 17፤2፤ሉቃ 9፤29
እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
የአ/ነ/ደ/ል/ቅ/ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት

comment