Sewaferawe Alene
ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ይህንን ቃል ደጋግመው ሲያነሱ እና እውነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስመስለው ፌስ ቡክ ላይ ሲለቁት ተመልክታችሁ ይሆናል፡፡ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለመቃወም እና ምእመኑን ከእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ለማውጣት እና ለዲያብሎስ ለማስረከብ በማሰብ ነው፡፡ቤተክርስቲያናችን ዘወትር እግዚአብሔርን በልቧ በተግባርና በአምልኮ ስርአቷ ትቀድሰዋለች /ታመሰግነዋለች/፡፡ቅዳሴ ማለት ምስጋና ማለት ነው ፡፡መናፍቃን ግን ለመተቸት ‹‹ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው››እያሉ ሲፎክሩና ሲሸልሉ በሀይማኖት ያልበሰሉትንም ሲያደናግሩ እንመለከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዳሴ/ጌታን ስለመቀደስ ምን ይላል እስቲ እንመልከተው፡፡
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
3፥15
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
8፥13
ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
የማቴዎስ ወንጌል
6፥10
ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ኦሪት ዘኍልቍ
20፥12
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል
11፥2
አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ታዲያ ቤተክርስቲያን ምን አጠፋች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባገኘችው ቃል ነው ቅዳሴ የምትቀድሰው/ጌታን የምታመሰግነው/
ለምትሰጡኝ አስተያየት መጽሀፍ ቅዱስ እንጂ ትችት እንዳይሆን
ጌታ ለመናፍቃኑ ልቦና ይስጣቸው
ምንም አስተያየቶች የሉም :
አስተያየት ይለጥፉ