የመናፍቃን ምላሽ


ጾምና መጽሀፍ ቅዱስ http://giorgiszeleda.blogspot.com/2013/08/blog-post_9.html
አማላጅነት
ምልጃ ማለት አንዱ ስለሌላው የሚያደርገው ልመናና ጸሎት ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ያስቀየመ በደለኛ፤ አንድም ጥፋቱን በመገንዘቡ ወይም ካስቀየመው ሰው በኩል የነበረውንና ሊኖረው የሚችለው ጥቅም ስለሚቀርበት ወይም ደግሞ ከዚያ ካስቀየመው ሰው ጋር በሰላም ካልኖረ ችግር ሊደርስበት ስለሚችል አስታርቁኝ ብሎ አማላጅ ይልካል፡፡ አማላጅ በመላክ ፈንታ ራሱ ሄዶ ይቅርታ የማይጠይቀው አንድም ያስቀየመውን ሰው ከማክበሩ የተነሣ በቀጥታ መሄድን እንደ እፍረት በመቁጠሩ ወይም ያን ሰው በጣም በማስቀየሙ እንዴትአድርጌዓይኑንለማየትእችላለሁ ብሎ በመፍራት ወይም ደግሞ ያ አማላጅ የሚላክበት ሰውበደረጃውከፍያለ ከመሆኑ የተነሣ በቀላሉ ሊያገኘው የማይችል በመሆኑ ነው፡፡ አማላጅ ሆኖ የሚላከው ሰው አግባብቶ እሺ ለማሰኘት ተሰሚነት ያለው ሰው መሆን ይኖርበታል፡፡
አማላጅነት ሦስት ነገሮችን (አካላትን) ይይዛል፡፡
ሀ) ተማላጅ (የሚለመን)፡- ተማላጅ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አምላክ ነው፡፡
“ከአንዱከእግዚአብሔር በቀርኃጢአትሊያስተሰርይማንይችላል?” (ሉቃ 5፡፳1)
ለ) አማላጅ (የሚለምን)፡- አማጅነት የፍጡር ሥራ ነው፡፡ አማላጆች ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ቅዱሳን በጸሎታቸው፣ በቃል ኪዳናቸው ከእግዚአብሔር ስለ በደለው ሰው ምሕረትን የሚያሰጡ ናቸው፡፡ (1ኛ ዜና ፳1፡07፣ ዘፍ 08፡፳3)
ሐ) የሚማለድለት (የሚለመንለት)፡- ኃጥኣን የቅዱሳን ምልጃና ቃል ኪዳን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ናቸው፡፡ (ኤር 7፡06-09፣ ዘኊ ፳1፡6-9)
አማላጅነት ያስፈለገበት ምክንያት
1. አማላጅነት የእግዚአብሔር ፈቃድና ትዕዛዝ በመሆኑ ነው፡፡
ጻድቃን ለኃጥኣን ወገኖቻቸው የሚለምኑት ልመና በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅና ተሰሚነት አለው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምንም እንኳን ኃጥኣንን በክፉ ሥራቸው ቢያዝንባቸውም በቸርነቱ የሚምርበት ምክንያት ይፈልጋልና የቅዱሳኑን ምልጃ ለዚሁ ቸርነቱ መንገድ ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ነው ኃጥኣንን በአማላጆች እንዲጠቀሙ የሚያዘው፡፡ ለምሳሌ፡-
ዘፍ. ፳፡1-06፡-ንጉሥ አቤሜሌክ የእግዚአብሔርን ሰው የአብርሃምን ሚስት ሊቀማው ባለ ጊዜ እንዲመልስ እግዚአብሔር ሌሊት በሕልም ሣራን እንዳይወስዳት የአብርሃም ሚስት ናትና እንዲመልስለት ካዘዘው በኋላ ንጉሡ አቤሜሌክ ይቅርታን በጠየቀው ጊዜ “ነቢይ ነው ስለ አንተ ይጸልያል ትድናለህም” በማለት እግዚአብሔር ስላዘዘው (ስለ ነገረው) ወደ አብርሃም ሄዶ እንዲጸልይለት ራሱ እግዚአብሔር መናገሩ ጻድቃን ለኃጥኣን አማላጆች እንዲሆኑ ፈቃዱ መሆኑን ያመለክተናል፡፡
ኢዮ. ፵2፡7-01፡-በኢዮብ ላይ ስለ ደረሰው መከራ ያጉረመርሙ የነበሩ ሦስቱን የኢዮብን ጓደኞች እግዚአብሔር አምላክ ሲናገራቸው “እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና. . .ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ. . .ባሪያ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል” ብሏቸዋል፡፡ ራሱ እግዚአብሔር ተገልጦ እያነጋገራቸው እያለ በቀጥታ ወደ እኔ ጸልዩ ይቅር እላችኋለሁ አላላቸውም፡፡ የኢዮብ አማላጅነት ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ኢዮብ እንዲሄዱ ነገራቸው እንጂ፡፡ እነርሱም እንደተዛዙት በአደረጉ ጊዜ ኢዮብ ስለ እነርሱ ጸለየ “እግዚአብሔርም የኢዮብን ፊት ተቀበለ”
2ኛ ቆሮ 5፡09-፳፡-እግዚአብሔር ወዳጆቹ ስለ ደከሙ እንዲለምኑት በእነርሱ የማማለድ ሥልጣን እንዳኖረ ሲገልጽ “በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” ነው ያለው፡፡ ይህም አማላጅነት የእግዚአብሔር ፈቃድና የቅዱሳን ሥራ (አገልግሎት) መሆኑን እንረዳበታለን፡፡
አማላጅነትእግዚአብሔርአምላክለሰውልጆችየሰጠውመጠቀሚያናቸርነቱንየማግኛመንገድነው፡፡አማላጅነትለሰውልጆችያስፈልጋልማለትሰዎችበቀጥታወደእግዚአብሔርመጸለይአይችሉምወይንምአይጸልዩምማለትአለመሆኑንከማናችንምየሚሰወርአይደለም፡፡
2. ከኃጥኣን ይልቅ የቅዱሳን ጸሎት የበለጠ የሚሰማ ስለሆነ ነው፡፡
“የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው፡፡ መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው፡፡ ጻድቃን ጮኹ እግዚአብሔርም ሰማቸው” (መዝ ፴3፤05)
“ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች” (ምሳ 0፡፳4፣ ምሳ 01፡፳3)
“የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው” (ምሳ 05፡8)
“እግዚአብሔር ከኃጥኣን ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል” (ምሳ 05፡፳9)
“የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች” (ያዕ 5፡06)
ለአቀራረብ እንዲያመች አማላጅነትን ለሁለት ከፍለን ልንመለከተው እንችላለን፡፡
1. አማላጅነት በአፀደ ሥጋ
እግዚአብሔር የሰዶምን ከተማና ሕዝቧን በኃጢኣታቸው ምክንያት ሊደመስሳቸው መሆኑን ለአብርሃም ነገረው፡፡ በዚህን ጊዜ አብርሃም በከተማው ውስጥ ሃምሳ ደጋግ ሰዎች (ጻድቃን) ቢኖሩ ከተማይቱን በሙሉ በመደምሰስ ደጎች ከክፉዎች ጋር አብረህ ታጠፋለህን? በማለት ምልጃውን ጀመረ፡፡ እግዚአብሔርም ሃምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ለሃምሳው ስል ከተማይቱን አላጠፋትም አለው፡፡ አብርሃምም ከእግዚአብሔር ጋር ንግግሩን በመቀጠል ደጋጎቹ ሰዎ አርባ አምስት፣ አርባ፣ ሠላሳ፣ ዐሥር ቢሆኑስ እያለ በከተማይቱ ውስጥ ዐሥር እንኳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን እንደማያጠፋ እግዚአብሔር ቃል ገባለት፡፡ ይሁን እንጂ ዐሥር እንኳን ደጋግ ሰዎች በከተማ ውስጥ ስላልተገኙ ከተማይቱ ተደምስሳለች፡፡ ይህ ታሪክ የሚያመለክተን እግዚአብሔር ምን ያህል የወዳጆቹን ምልጃ የሚቀበል መሆኑን ነው (ዘፍ 08፡፳2-፴3)፡፡
የእስራኤል ሕዝብ ጣዖት ሠርቶ በማምለክ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ሕግ ባፈነገጠ ጊዜ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከእርሱ ጋር ለነበረው ለሙሴ ምን እንዳለውና ሙሴም በአማላጅነቱ እንዴት አድርጎ ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረትን እንዳስገኘ ራሱ ሙሴ ሲገልጽ “እግዚአብሔርም ሙሴን እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው፡፡ ... እንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው፡፡ ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፣ አለም፡- አቤቱ ቁጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብጽ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለምን ተቃጠለ?. . .ከመዓትህ ተመለስ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ. . .በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ፡፡ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ” (ዘጸ ፴2፡9-04፣ ±ç9፡08-09፣ 1ኛ ነገ 03፡1-0፤ 1Ñ07፡1-07፣ 2Ñ08፡፴-፵፣ 2ኛ ነገ 04፡08)
አንድ መኮንን ሰው ስለ ሞተች ልጁ ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቦ ተንበርክኮ ለምኖታል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶም ልጁን ከሞት አንሥቶለታል (ማቴ 9፡08-፳5)፡፡
ቅዱስ እስጢኖስ በወገሩት ጊዜ ለሚ¨ግሩት ሰዎች ሲጸልይ “ጌታ ሆይ ይህን ኃጢኣት አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ (ሐዋ 7፡፷)፡፡
“ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ” ጻድቃን በምልጃቸው፣ በጸሎታቸው እንጂ ሰዎችን በምን ሊጠብቁ ይችላሉ? ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት ሳይሆን በጻድቃን ሊጠበቅ እንዲችል ንጉሥ ዳዊት ገልጾልናል (መዝ ፻፵1፡7፣ ምሳ 01፡0)
2. አማላጅነት በአፀደ ነፍስ
አማላጅነት በአፀደ ነፍስ (ሥጋና ነፍስ ከተለዩ፤ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ) ከማየ ታችን በፊት ስለ ነፍስና በነፍሳቸው ስላላቸው ዕውቀት በተወሰነ መልኩ ለማየት እንሞክራለን፡፡
1. “ነፍስ” በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ትገለጣለች
ሀ) ነፍስ ሲባል እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በአፍንጫው እፍ ያለበት መለኮታዊ እስትንፋስ በመሆኑ ከሥጋ ተለይቶ የሚወጣ ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሔር የሚመለስ ነው፡፡
“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” (ዘፍ 2፡7)
“ሁሉ አፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል፡፡ የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እንደምትወጣ የእንስሳት ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እንደምትወርድ የሚያውቅ ማን ነው” (መክ 3፡፳)
“አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ” (መክ 02፡7)
“ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ” (መዝ ፻3፡፳9)
“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” (ማቴ 0፡፳8)
“እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር” (ሐዋ 7.፶9) እግዚአብሔር ምንም የማያስተውል የማይሰ ማን የማይናገር በድን ነፍስ አይቀበልም፡፡
“በሥጋ ሞት በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው” 1ኛ ጴጥ 3፡09)፤
(ኢዮ 09፡፳6-፳7፣ ማቴ. ፳7 ፶2-፶4፣ ሉቃ. ፳3፡፵3 ከዚህ በተጨማሪ እንደየሁኔታው የተለያየ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡
ለ) ነፍስ ሲባል የእንስሳት ሕይወት ለመሆኑ
“እግዚአብሔርም አለ ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ታገኝ” (ዘፍ 1፤፳)
“የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና” (ዘሌ. 07፡01፣ ዘፍ. 9፡4-7)
ሐ) ነፍስ ሲባል ስሜት ማለት ለመሆኑ
“የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች” (1ኛ ሳሙ 08፡01)
“ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች” (ሉቃ 1፡፵7)
መ) ነፍስ ሲባል ሰው ወይም ሰውነትን የሚያመለክት ለመሆኑ
“በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ” (ኢያ 01፡01፣ ሕዝ 08፡4)
“ነፍሴን በጾም አደከምኋት” (መዝ. ፴4፡03 መዝ ፵1፡4፣ መዝ ፻5፡05)
“ያንም ነቢይ የማትሰማ ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋ ለች” (ሐዋ 3፤፳3)
2. ቅዱሳን በሥጋ ቢሞቱም በነፍስ ሕያዋን ናቸው
ቅዱሳን የሆኑትን ጻድቃን፣ ሰማዕታትን፣ ነቢያት ሐዋርያትን ከእንቅልፍ ሥጋ በኋላ ሙታን (አንዳች የማያውቁ) ማለት አንችልም፡፡ በሥጋ ቢያንቀላፉም (ቢሞቱም) ሕይወተ ነፍስ ስላላቸው ሕያዋን ናቸው፡፡
ቅዱሳን በሥጋ ቢሞቱም (ቢያንቀላፉም) በነፍስ ሕያዋን እንደሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ ሲገልጽ “የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን” ብሏል፡፡ (2ኛ ቆሮ 6፡9)
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰዱቃውያን ጋር ይነጋገር በነበረ ጊዜ ከዓመታት በፊት የሞቱትን የአብርሃምን፣ የይስሐቅን፣ የያዕቆብን ሕያውነት ሲገልጽ “እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ. . .የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይደለሁም” (ማቴ ፳2.፴1-፴2፣ መዝ ፻5፡6)
“ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለጠጋ ሰው ነበር፡፡ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር፡፡ አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሃ በቁስል ተወርሶ በደጅ ተኝቶ ነበር፡፡ ከባለ ጠጋው ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳን መጥተው ቁስሎቹን ይልሱ ነበር፡፡ ደሃውም ሞተ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፡፡ ባለጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ፡፡ እርሱም በስቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ፤ አልዓዛርም በአብርሃም እቅፍ እርሱም እየጮኸ፡፡ አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ፣ በዚህ ነበልባል እሰቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልን አልዓዛርን ስደድልኝ አለ፡፡ አብርሃም ግን አንተ በሕይወት ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም ክፉ፡፡ አሁንግንእርሱበዚህይጽናናልአንተምትሣቀያለህ፡፡ ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል አለ፡፡ እርሱም፡- እንኪያስ አባት ሆይ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፡፡ አምስት ወንድሞ አሉኝና እነርሱም ደግሞ ወደዚህ ስቃይ ሥፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው አለ፡፡ አብርሃም ግን፡- ሙሴንና ነቢያት አሉላቸው እነርሱን ይስሙ አለው፡፡ እርሱም፡- አይደለም አብርሃም አባት ሆይ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ፡፡ ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፣ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው፡፡” (ሉቃ 16፡09-፴1) በዚህ ጥቅስ ላይ የአብርሐም ሕያውነት በግልጥ እንመለከታለን፡፡
ምክንያቱም አብርሃም ከባለጠጋው ጋር ሲነጋገር መታየቱ የአብርሃምን ሕያውነት ይገልጽልናል፡፡ ሕያው ያልሆነ፣ የሌለን ነገር ሊያዩት፣ ሊያነጋግሩትና ሊለምኑት አይቻልምና፡፡ ይህ የጌታችን ትምህርት ምሳሌ ሳይሆን እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ምክንያቱም ምሳሌ ቢሆን ኖሮ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ምሳሌዎች ሲያቀርብ ስም ሳይጠቅስ “አንድ ሰው” እንደሚል ሁሉ፤ ይህንንም ታሪክ ስም ሳይጠቅስ በተናገረ ነበር፡፡ ነገር ግን የአልዓዛርን፣ የአብርሃም፣ የሙሴንና በጠቅላላው ነቢያትን ጠቅሷል፡፡ ደግሞም ምሳሌ በፍጥረታት በሌለ ነገር መቼም ቢሆን ሊመሰል አይችልም፡፡
በማቴ 07፡2-4 በሥጋ ከሞተ ብዙ ጊዜ የሆነው ሙሴ ሞተ ሥጋን ካልቀመሰው (ካረገው) ከኤልያስ ጋር ሆነው ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቅዱስ ተራራ ሲነጋገሩ መታየታቸውን “እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩቸው” በማለት ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት መታየታቸውን ቅዱስ መጽሐፍ አስፍሮታል፡፡ ይህ የሚያሳውቀን ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ ሕያዋን መሆናቸውንና ሞተ ሥጋ ሙሴን እንደ ኤልያስ ከመገለጥና ከመናገር እንዳልከለከለው ነው፡፡
“አምስተኛውም ማኅተም በተፈታ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎችን ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፡- ቅዱስናእውነተኛጌታሆይ፥እስከመቼድረስአትፈርድምደማችንንስበምድርበሚኖሩትላይእስከመቼአትበቀልም? አሉ፡፡ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው” (ራእ 6፡9-01) ቅዱሳን ሰዎች በሥጋ ቢሞቱም በነፍሳቸው ሕያዋን በመሆናቸው ነው የታዩት፤ ከእግዚአብሔር አምላክ ጋርም የተነጋገሩት፡፡
3. ቅዱሳን እውቀታቸው (በሥጋና በነፍስ)
እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱሳኑ ስውር የሆነውን ነገር ሁሉ ገልጾ ያሳውቃቸዋል፡፡ ቅዱሳኑም እግዚአብሔር በሰጣቸው ዕውቀት የተነሣ በሥጋ በዚህ ዓለም ባሉበትም ጊዜ ሆነ በነፍስ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ ስውሩን ግልጹን ያውቃሉ፡፡
በ2ኛ ነገሥ 5፡፳-፳5 ነቢዩ ኤልሣዕ በዚህ ዓለም በነበረ ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ በምሥጢር ከሶርያዊው ንዕማን ስጦታን መቀበሉን ሳይሰማ እግዚአብሔር ገልጦለት አወቀ፡፡
በ2ኛ ነገ. 6፡02 ከሶርያ ንጉሥ ባለሟሎች አንዱ ለንጉሡ ስለ ኤልሳዕ ምሥጢር አዋቂነት ሲገልጽ “ጌታ ሆይ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል”
በ2ኛ ዜና ፳1፡02 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮራም ብዙ ኃጢኣት በመሥራቱ ከዓመታት በፊት በእሳት ሰረገላ ወደ ሰማይ ተወስዶ የነበረው ነቢዩ ኤልያስ የተግሣጽና የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደላከለት ይገልጽልናል፡፡
በ2ኛ ሳሙ ፳8፡3-09 ነቢዩ ሳሙኤል ከሞተ በኋላ የሳኦልን ጥፋቱን ተረድቶ ወደፊት የሚደርስበትን ችግር አውቆ ዘርዝሮ አስረድቶታል፡፡ ነቢዩ ሳሙኤል ሞተ ሥጋ የሳኦልን የወደፊት ሁኔታ ከማወቅ አልከለከለውም፡፡
በሐዋ 5፡3-9 ሐዋርያው ጴጥሮስም የሐናንያንና የሰጲራን ምሥጢራዊ ስምምነት እግዚአብሔር ገልጾለት አውቆል፡፡
በሉቃ 9፡09-፴1 ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር ተራራ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን በገለጸበት ወቅት ወደፊት በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ሁኔታ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መነጋገራቸው ሞተ ሥጋ ወይንም ከዚህ ዓለም መለየት (ማረግ) በምድር ስለሚደረገው ነገር ከማወቅ እንዳልከለከላቸው ያስረዳል፡፡ “ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ ይነጋገሩ ነበር” እንዲል፡፡
ከላይ በሉቃ. 06:09-፴1 በጠቀስነው ጥቅስ እንደምንረዳው አብርሃም የኖረው ከሙሴ ከሌሎች ነቢያት መነሣት በፊት ቢሆንም፤ አብርሃም ለባለ ጠጋው “ሙሴና ነቢያት አሉላቸው” ማለቱ ሙሴ የተባለ ነቢይና ሌሎች ነቢያት መነሣታቸውን በማወቁ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አብርሃም፤ አልዓዛር የሚባል ሰው በድህነት መኖሩንና ባለጠጋው ሰው ደግሞ በክፋት መኖሩን አውቋል፡፡ ይኸውም “ልጄ ሆይ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ” ባለው አነጋገሩ ይታወቃል፡፡
1ኛ ቆሮ. 03፡02-03 “ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደታወቅሁ አውቃለሁ” ማለቱ በዚህ ዓለም የማውቀው፣ በወዲያኛው ዓለም ከማውቀው ያነሰ ነው ሲል ነው፡፡
“ዛሬስ በመስተዋት ለድንግዝግዝ እንደምናይ ነን” ማለቱ መስታወት ፊትን ካሳየ ጀርባን አያሳይምና በዚህ ምድር ሳለ ሁሉን ማወቅ አለመቻሉ ሲገልጽ ነው፡፡ “በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን” ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ ሁሉ ተገልጦላቸው በምድር ከሚያውቁት በበለጠ ሁኔታ እንደሚያውቁ ሲያመለክት ነው፡፡ “ዛሬስ በእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደታወቅሁ አውቃለሁ” ማለቱ በዚህ ዓለም የማውቀው በወዲያኛው ዓለም ከማውቀው ያነሰ ነው ሲል ነው፡፡
4. የቅዱሳን አማላጅነት በአፀደ ነፍስ
የቅዱሳን ሞታቸው ዕረፍታቸው ነውና በእግዚአብሔረ ፊት የከበረ ነው (መዝ ፻05፡05) ይህ ዕረፍታቸው ከሕያውነት ወደ ምውት፣ ከአዋቂነት ወደ አላዋቂነት የሚወስዳቸው ሳይሆን በዚህ ዓለም ከተሰጣቸው ጸጋ ወደ ሚበልጥ ክብር የሚሸጋገሩበት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን ምን እንድመርጥ አላስታውቅም፡፡ በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው” በማለት እንደገለጸው በሥጋ መሞት ለቅዱሳን ወደ ተሻለው ክብር ወደ በለጠው ቦታ መሄድ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ (ፊልጵ 1፡፳1-፳4)
ቅዱሳን ከዕረፍታቸው (ከሞታቸው) በኋላ በዚህ ዓለም ያደርጉት እንደነበረው በጾምና በጸሎት በስግደት እንዲሁም ልዩ ልዩ መከራ መቀበል ባይኖርባቸውም በዚህ ዓለም ሳሉ የሠሩት ትሩፋትና የተቀበሉትን ቃል ኪዳን እያሰቡ በጸሎታቸው የሚታመኑትንና ስማቸውን የሚጠሩትን ሰዎች ሲረዱበትና ለክብር ሲያበቁበት ይኖራሉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ከሞተ በኋላ በምድር የነበረው ሥራቸው እንደሚከተላቸው ሲገልጽ “ከሰማይ፡- ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹዓን ናቸው፡፡ መንፈስ፡- አዎን ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁኝ” (ራእ 04፡03) በተጨማሪም ቅዱስ ጳውሎስ ስለ አቤል ሲመሰክር “እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል” ብሏል፡፡ (ዕብ 01፡4)
የያዕቆበ ወንድሙ ይሁዳ ጠቅሶ ያስተማረበት መጽሐፈ ሄኖክ ስለ ቅዱሳና በአፀደ ነፍስ አማላጅነት ሲገልጽ “በእነዚህ ወራት በሰማይ የሚኖሩ ጻድቃን በአንድ ቃል ሆነው ተባብረው ያመሰግናሉ፡፡ በሰው ፈጽመው ይለምናሉ፤ ፈጣሪያቸውንም ያመሰግናሉ” (ሄኖ 02፡፴4፣ ይሁዳ 1፡04-05 እና ሄኖ 1፡9)
2ኛ ነገሥ 03፡@1 የነቢዩ የኤልሳዕን ታላቅነትና ክብር ያወቁ ሰዎች በጦርነት ጊዜ የሞተባቸው ሰው በድኑን አምጥተው በነቢዩ መቃብር ላይ ሲጥሉት የኤልሳዕ አጽም ከሞት አስነሥቶለታል፡፡ ፈጣሪውን ያገለገለ አጽም ስለሆነ የከበረና አሁንም ሥራ የሚሠራ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ነቢይ የተቀበረ አጥንቱ እንኳ ሙት የሚያስነሣ ከሆነ ከነፍሱማ ምንኛ ታላቅ ተአምር ታደርግ፡፡
ኤር. 05፡1 “እግዚአብሔርምእንደዚህአለኝ።ሙሴናሳሙኤልበፊቴቢቆሙም፥ልቤወደዚህሕዝብአይዘነብልምከፊቴጣላቸውይውጡ”የዚህ የአምላክ ገለጻ በሚደረግ ላይ የተንተራሰ እንጂ በማይደረግ ላይ አይደለም፡፡ ቅዱሳኑ ለሰዎች በፊቱ እንደሚቆሙ ተናገረ፡፡ ነገር ግን ኤርምያስን አንድ ጊዜ ፍርድ ስላስተላለፈባቸውና ልባቸው የማይመለስ መሆናቸውን ሲገልጽለት ከቁጣው እንደማይመለስና እንደተጣሉ አስረዳው፡፡ በዚህም ከምድር የተለዩ ሙሴንና ሳሙኤልን ስማቸውን መጥራቱ በፊቱ እየቆሙ አሁንም የሚጸልዩ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡
2ኛ ጴጥ 1፡03-05 “ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁ፡፡ ከመውጣቴም በኋላ እነዚህ ነገሮች እንድታስቡ በጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁኝ፡፡” በዚህ ማደሪያ ሳለሁኝ ማለቱ በዚህ ዓለም ስኖር በሥጋዬ ማለቱ ነው፡፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና” ያለው እግዚአብሔርን በሞቱ እንዴት እንደሚያከብር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመልክቶት ነበርና ነው፡፡ “አንተ (ጴጥሮስ) ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደ ምትወደው ትሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደ ማትወደውም ይወስድሃል አለው፡፡ በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔር ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህ አለ” እንደተባለ፡፡ (ዮሐ. ፳1፡08-09) “ከመውጣቴም በኋላ እነዚህ ነገሮች እንድታስቡ የጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ” በማለቱ ከዚህ ዓለም ከተለየ በኋላ ምእመናን ልጆቹ ለጸጋና ለክብር እንዲበቁ ለማሳሰብ እንደሚተጋ ሲገልጽ መሆኑን እንረዳበታለን፡፡
ራእ. 6፡9-01 እንደተገለጠው በሰማይ ከመሠዊያው በታች ያሉት ነፍሳት መከራ ባደረጉባቸው ሰዎች ላይ አምላክ ፍርድ እንዲሰጣቸው ከጸለዩባቸው ስማቸውን በመጥራት የተሰጣቸውን ቃል ኪዳን ማዘከር ከፈጣሪያቸው ምሕረትና ይቅርታን እንዲደረግላቸው (እንዲሰጧቸው ለሚፈልጉ) መናገር (መጸለይ) አይችሉም ብሎ ማሰብ ፍጹም ክህደት መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡
5. የቅዱሳን ቃል ኪዳን አማላጅ ሆኖ ያገለግለናል
እግዚአብሔር አምላክ በሥጋ ሳሉ ያገለገሉትንና ያስደሰቱትን ባለሟሎቹን ከዕለተ ሞታቸው በኋላ የሚያገለግል ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን እያሰቡ የሚለምኑትን ይቅር ሲላቸው ይኖራል፡፡
መዝ ፹8፡3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ከተመረጡት ሰዎች ጋር የሚደረገው ቃል ኪዳኑ ለዘላለም እንደሆነ ሲገልጽ “የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ለዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ጽድቁም በልጅ ልጆቹ ላይ ነው ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ፣ ትእዛዙንም ያደርግ ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው” (መዝ ፻2፡ 07-08) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ወደዳቸው” (ዮሐ 03፡1-2)
እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ሲማጸኑት ምሕረትን ለሕ ዝብ ሲያደርግላቸው እናያለን፡፡ ዘፍ 07፡04 “እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለትና እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመለስ ፍጹምም ሁን ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፤ እጅግም አበዛሃለሁ” አለው፡፡ እንዲሁም በዘፍ ፳2፡08) “የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ” በማለት እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሐም ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡ ነቢዩ ሙሴም በአባቶቹ የተገባውን ቃል ኪዳን ተጠቅሞ አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ” ብሏል፡፡ “እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ” (ዘጸ 2፡፳4) ተብሏል፡፡
2ኛ ነገ 03፡፳2-፳3 ከሶርያ ንጉሥ አዛኤል እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እንዳዳናቸው ሲገልጽ “እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፣ ማራቸው፣ ከአብርሃምና ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ ሊያጠፋቸው አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም” ይላል፡፡ ምን ያህል የቅዱሳኑን ቃል ኪዳን ጠቀሜታ እንዳለው፣ እንዴት ሰዎችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን እንደሚያሰጥ ያስረዳናል፡፡
ምንም እንኳን እስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ተገልጦለት ባዕዳን አማልክት እንዳያመልኩ ያዘዘው ቢሆንም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም ይልቁንም ከእግዚአብሔር እየራቀ ሄደ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቆጣ እንዲህም አለው፡- “ይህን ሠርተሃልና ያዘዝሁህንም ቃል ኪዳኔንና ሥርዓቴን አልጠበቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ቀዳድጄ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ፡፡ ነገር ግን ከልጆችህ እጅ እቀደዋለሁ እንጂ ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘመንህ አላደርግም” (1ኛ ነገ 01፡01-03)
ሉቃ 1፡፶4 “ለአባቶቻችን እንደተናገረ ለአብርሃምና ለዘሩ የዘላለም ምሕረቱን አሰበ፡፡ እስራኤልን በብላቴናው ረድቷል” በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን አሰበ፡፡ እስራኤል ዘነፍስን እንደረዳ በጸለየችው ጸሎት ተናግራለች፡፡ በተጨማሪም (2ኛ ነገ 09፡፴4) ተመልከቱ፡፡
በአጠቃላይ፡- ምልጃ የሐዋርያት ትምህርት ነው፡፡ ሐዋርያት በመልእክታቸው፣ በትምህርታቸውና በተግባራቸው ስለ ምልጃ አስፈላጊነት አስተምረዋል፡፡
1ኛጢሞ2፡1-2 “ልመናና ጸሎት ምልጃም፣ ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ ፊት እመክራለሁ”
ፊልጵ4፡02 ”በእግዚአብሔርፈቃድሁሉተረድታችሁናፍጹማን ሆናችሁእንድትቆሙ፥ሁልጊዜስለእናንተበጸሎቱይጋደላል”
1ኛ ተሰ5፡፳5 “ወንድሞቼ ሆይ ስለ እኛ ጸልዩ”
1ኛ ቆሮ 9፡04-05 “ራሳቸውምስለእናንተሲያማልዱ፥በእናንተላይከሚሆነውከሚበልጠውከእግዚአብሔርጸጋየተነሣይናፍቁአችኋል”
ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን!!!

ምንም አስተያየቶች የሉም :

አስተያየት ይለጥፉ

comment