ሰንበት ት/ቤት




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲ ነጌሌ ደ/ልዳ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ለሰንበት ት/ቤቶች በወጣው አመሰራረትና አደረጃጀት መመሪያ መሰረት በ1970 ዓ/ም ተመሰረተ፡፡
ሰ/ት/ቤቱ ባሳለፋቸው 34 ዓመታት ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡ በተለያዩ ግዜያት ከውጪ መናፍቃን ሰርገው በተለያዩ ሁኔታዎች ሰርገው እየገቡ መሰረቱን ለመናድና ወጣቱን ለማስኮብለል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
በተለይ ከ1987-1989 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ዓመታትውስጥ ቀላል የማይባሉ አባላቱን በወቅቱ በነበረው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ቢያጣም ከዘጠና ዓ/ም ጀምሮ ግን በእግዚአብሔር እርዳታ ወጣቶችንና ምዕመናንን በእግዚአብሐየር ቃል በማነጽና በማስተማር እስከ ዛሬ ድረስ የዘለቀ ዓመታዊ የከክረምትና የሳምንት የት/ም መርሐ-ግብር በማዘጋጀት ወጣቶችን በክረምት የ3 ወራት ተከታታይ ት/ም በማስተማርና በሰርተፍኬት በማስመረቅ፤ከደብሩ ሰበካ ጉባኤና ስብከተ ወንጌል ጋር በመሆን የተለያዩ ታላላቅ መንፈሳዊ ጉባኤያትን በዓመት ከ3 ጌዜያት በላይ በማዘጋጀት የከተማውን  ምዕመናን ከማስተማር ባሻገር ከዚህ በፊት በመናፍቃን ተነጥቀው የነበሩ ምዕመናንንና ወጣቶችን ለመመለስ ችሏል እንዲሁም በከተማው አዋሳኝ በሆኑ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሰ/ትቤት አገልጋዮችን በመላክ ሲያስተምር ቆይቷል….
በቀጣይ የሰ/ትቤቱን ሙሉ መረጃ እናደርሳችኋለን፤
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡













ምንም አስተያየቶች የሉም :

አስተያየት ይለጥፉ

comment