መጋቢት 27 ጥንተ ስቅለቱ ለኢየሱስ ክርስቶስ
በዚህ ገጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አሰተምህሮን የጠበቁ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት(ዶግማ) እና ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን(ቀኖና) እንዲሁም የቤተ ክርስቲያናችን ቱፊቶች የምንማርበትና የምንዘክርበት ይሆናል፡፡
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከወደቀበት የኃጢያት አዘቅት ሊያወጣው ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ነስቶ ሳይገባው በበረት ተወልዶ ፤ ስደታችንን ሊያስቀር ሳይገባው ተሰዶ፤ በክፉዎች አይሁድ ምክር ተከሶ በባህርይው መንገላታት የማይገባው አምላክ ለኛ ሲል የተንገላታና የተደበደበ ፤በጥፊ የተመታ ፤የተዘባበቱበት፤ ምራቅ የተተፋበት እርጥብ መስቀል ተሸክሞ ከሄሮድስ ወደ ጲላጦስ እየተመላለሰ ከዚያም በቀራንዮ የራስ ቅል በምትባል ሥፍራ ተሰቅሎ ለኛ ሲል ሞታችንን በሞቱ ሽሮ በዋጋ ገዝቶናል /ማቴ. 27፣1 ፤ማር.15 ፣1 ፤ሉቃ. 23፣1 ፤ ዮሐ.19፣ 1 /
ይህን ሁሉ መከራ የከፈለው እኛን ከሰይጣን ግዞት ባርነት ነጻ ለማውጣት ነውና ውለታውን ልንከፍል የምንችለው ስለሞቱ በማሰብና በማልቀስ ብቻ ሣይሆን በደሙ የተዋጀንና ዋጋ የተከፈለብን ነንና ዘወትር በጾምና በጸሎት በመትጋት ራሳችንን ከሃጥያት ግብር በመጠበቅና ስለተከፈለልን ዋጋ በማወደስ ጭምር ሊሆን ይገባል፡፡
መጋቢት 27 ጥንተ ስቅለቱ ለኢየሱስ ክርስቶስ
የመስቀሉ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
አ/ነ/ደ/ል/ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት

ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኩሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘያስተርኢ ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ አብ ዋህድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅያዊ ዘሠረጸ እም አብ ፡፡ ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን እንተ ላእሌ ኩሉ ጉባዔ ዘሐዋርያት፤ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ሀጢያት ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ለዓለመ አለም አሜን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም :
አስተያየት ይለጥፉ