ሰኞ 24 ኖቬምበር 2014

ጾመ ነብያት(የገና ጾም

“ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥”

ጾም በብሉይ ኪዳን
ት.ዳን 10፤2
“በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም”።
ት.ኢዩ 2፤15
“ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥”
መዝ.108 (109) ፤24
“ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ”።
ኢያ.7፤6-9 ፤አስ 4፤16፤2ኛ ሳሙ.12፤17፤ዘዳ 9፤9-18፤ ዘዳ10፤10፤1ኛ ነገ.19፤6-10፤
ጾም በሀዲስ ኪዳን
ማር 9፤29
“ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው”።
ማቴ.6፤16
“ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል”።
ሉቃ. 6፤21
“እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና”።
የሐዋ.ሥራ 13፤3
“በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው”።
በዚህ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት በቤተ ክርስቲያናችን በአዋጅ የሚጾሙ ሰባት አጽዋማት አሉ፤
እነዚህም፡- 1.አብይ ጾም 2.ጾመ ሐዋርያት 3. ጾመ ነብያት(የገና ጾም) 4. ጾመ ፍልሰታ 5.ጾመ ድኅነት(አርብና ረቡዕ) 6.ጾመ ነነዌ 7.ጾመ ገሀድ(በጥምቀት ጥር 10 ቀን የሚጾም) ሲሆኑ ፡-
ከነዚህ መካከል የነብያት ጾም ጾመ ስብከትም ይባላል አበው ነብያት በትንቢት የክርስቶስን መምጣት ከመስበክ ባለፈ አምነው የሰበኩት ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ በጾምና በጸሎት ይማጸኑ ነበር ቃሉን የማይጥፈው እግዚአብሔር አምላክም አንድያ ልጁን ልኮ ዓለምን በልጁ በክርስቶስ በደሙ ዋጅቷል፡፡ አሁን እኛም ምዕመናን የአበውን ፈለግ በመከተል ይህንን ጾም እንጾማለን ፡፡ የ2007 ዓ/ም ጾመ ነብያት ከህዳር 15-29 ይጾማል ፤እግዚአብሔር ከጾሙ በረከት ያሳትፈን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ምንም አስተያየቶች የሉም :

አስተያየት ይለጥፉ

comment