ጾም
ጾም ማለት ከእህል እና ከውሃ እንዲሁም ከስጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው። ጾም
ማለት በጾም ወቅት ስጋ ነክ ምግቦችን ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ አይነቶችን መለወጥ ብቻ ሳይሆን
የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ነው።።
ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን
ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው። ጾም ለ እግዚአብሔር ያለንን
ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው ስለዚህ ይህን አብይ ጾም ስንጾም፤ አይናችን ትፁም (ክፉ ከማየት)፤ ጆሮም ትፁም
(ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤ እጅም ትፁም( ከመስረቅ ሆነ
ሰውን ከመደብደብ) ፤ አግርም ትፁም (ከሃጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤ ሁላችንም በተሰበረ ልብ
ሆነን እንፁም። አሁን ያለንበት ወቅት አብይ ጾም ይባላል። አብይ ማለት ታላቅ ማለት ነው። ይህ ጾም ታላቅ ጾም ያሰኘበት
ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙ እና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ
ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው
ጾም ነው። የመጀመሪያው የአብይ ጾም ሳምንት ዘወረደ ይባላል። ይህም ዘወረደ ማለት የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ፈቃዱ
ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም
የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13፡፡
ቀዳማዊው
አዳም የፈጣሪውን
የእግዚአብሔር የጾም ትእዛዝ በማፍረሱ ምክንያት ገነትን ከመሰለ ቦታ እግዚአብሔርን ከመሰለ ቅዱስ አምላክ ጌታ ጋር ተለያየ። ስለዚህም በጾም ምክንያት የፈጣሪውን ሕግ አፍርሶ የጠፋውን ቀዳማዊውን አዳም ለማዳንና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ
ሲል የሰውን ልጅ ለመፈለግ የመጣው ዳግማዊው አዳም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ሥራውን የጀመረው በጾም ነበር
(ማቴ 4፥1-11)።
ዳግማዊው
አዳም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ሐጢአት የሌለበት፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ፣ ፍጥረታትን በቃሉ የፈጠረ፤ ሁሉ በእጁ የሆነ፤
ድንቅ መካር ሃያል አምላክ ሲሆን ምንም እንደሌለው ተራበ፤ ይህም ለእኛ ምሳሌ ይሆነን ዘንድ ነው። የነቢያት አምላክ ነውና፤
ኦሪትንና ነቢያትን ሊፈጽም እንደ ነቢያቱ 40 ቀንና 40 ሌሊት በገዳም አደረ፤ በዲያቢሎስ ተፈተነ፤ ይህም ለእኛ ምሳሌ ይሆነን
ዘንድ ነው። ከነቢያት መካከል እንደ እነ ሙሴ ጽላቱን ከፈጣሪው ዘንድ ከመቀበሉ በፊት እንዲሁ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሟል፤
ምንጊዜም ቅዱሳን አባቶቻችን አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊት
ቅድሚያ ይጾሙ ነበር። ሐዋርያትም ቢሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት በጾም ነበር ፈጣሪያቸውን የሚጠይቁት፤ ፈጣሪያቸውም የለመኑትንና የሚሹትን ይሰጣቸዋል። የዚህ አይነቱ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሐዋርያት በአገልግሎታቸው የጸኑና የበረቱ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ስለዚህ እኛም ዛሬ ጌታችንን፤ ቅዱሳን ነቢያትን፤ እንዲሁም ቅዱሳን ሐዋርያትን ምሳሌ አድርገን ራሳችንን ለፈጣሪ ሰጥተን እንጹም። በዚህ በመጀመሪያ ሳምንት እያንዳንዱ ክርስቲያን ለጾም ምን ያህል መዘጋጀት እንዳለበት ያውቃል ይረዳልም ስለዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን ለፈጣሪያቸው ታምነው ጾሙን ከምግባር ጋር እንደጾሙት ሁሉ እኛም ልክ እንደ አባቶቻችን ይህን ታላቅ ጾም ከምግባር ጋር ለመፈጸም እርሱ ፈጣሪያችን ይርዳን። ለመጾም ቅድሚያ ሁኔታ ምን እንደሆን ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና፤ ሰዎች ከታላቅ አክብሮት ጋር ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው እና ሕገ እግዚአብሔርን ፈጽመው እንዲሁም ደግሞ የቀደመውን እባብ ሰይጣን ዲያብሎስን በጾም ረትተው ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመሸጋገር የሚያስችለውን ጎዳና የሚያዘጋጁበት ጊዜ ነው። ጾሙ የበረከት ይሁንልን አሜን።

በዚህ በመጀመርያው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት
ወተሐሰዩ ሎቱ በረአድ
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር
በአማርኛ፦
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ። (መዝ.፪፡፲፩-፲፪)
ከመምህር ለማ በሱፍቃድ ገጽ የተወሰደ
ምንም አስተያየቶች የሉም :
አስተያየት ይለጥፉ