ጾም በብሉይ ኪዳን
ት.ዳን 10፤2
“በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም”።
ት.ኢዩ 2፤15
“ በጽዮን መለከትን ንፉ፥
ጾምንም ቀድሱ፥
ጉባኤውንም አውጁ፥”
መዝ.108 (109) ፤24
“ጕልበቶቼ በጾም
ደከሙ፤ ሥጋዬም
ቅቤ በማጣት
ከሳ”።
ኢያ.7፤6-9
፤አስ 4፤16፤2ኛ ሳሙ.12፤17፤ዘዳ 9፤9-18፤ ዘዳ10፤10፤1ኛ ነገ.19፤6-10፤
ጾም በሀዲስ ኪዳን
ማር 9፤29
“ይህ ወገን
በጸሎትና በጦም
ካልሆነ በምንም
ሊወጣ አይችልም
አላቸው”።
ማቴ.6፤16
“ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች
አትጠውልጉ፤ ለሰዎች
እንደ ጦመኛ
ሊታዩ ፊታቸውን
ያጠፋሉና፤ እውነት
እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን
ተቀብለዋል”።
ሉቃ. 6፤21
“እናንተ አሁን
የምትራቡ ብፁዓን
ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ
ብፁዓን ናችሁ፥
ትስቃላችሁና”።
የሐዋ.ሥራ 13፤3
“በዚያን
ጊዜም ከጦሙ
ከጸለዩም እጃቸውንም
ከጫኑ በኋላ
አሰናበቱአቸው”።
በዚህ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት በቤተ ክርስቲያናችን በአዋጅ የሚጾሙ ሰባት አጽዋማት
አሉ፤
እነዚህም፡- 1.አብይ
ጾም 2.ጾመ ሐዋርያት 3. ጾመ
ነብያት(የገና ጾም) 4. ጾመ ፍልሰታ 5.ጾመ ድኅነት(አርብና ረቡዕ) 6.ጾመ ነነዌ 7.ጾመ
ገሀድ(በጥምቀት ጥር 10 ቀን የሚጾም) ሲሆኑ ፡-
ከነዚህ መካከል ጾመ ፍልሰታ በዚህ ወቅት ከነሐሴ1-16
በየዓመቱ የሚጾም ሲሆን ይህን ጾም ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን
ሐዋርያት ናቸው፤
ይኸውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ54 ዓ/ም ገደማ በጥር 21 ቀን አርፋ ሐዋርያት ሊቀብሯት ሲሔዱ አይሁድ
ይበትኗቸዋል ፤ከስምንት ወራት በኋላ በነሐሴ ወር ቀብረዋታል፡፡ በዚህ ግዜ ቶማስ ስታርግ አግኝቷት ሰበኗን እንደሰጠችው የውዳሴ
ማርያም ትርጉም ይናገራል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ጋር ደርሶ ትንሳኤዋን እንዳየ ከገለጸላቸው በኋላ እኛስ ትንሳኤዋን ሳናይ እንዴት
እንቀራለን ሲሉ ከነሐሴ 1-16 በጾምና በጸሎት ተወስነው ሱባዔ ከገቡ በኋላ ትንሳኤዋን ለማየት ችለዋል ፡፡ እኛም የሐዋርያትን
ፈለግ በመከተልና እንደ ቶማስ ከትንሳኤዋን በረከት ለመካፈል እንጾማለን
፡፡
እግዚአብሔር ከመቤታችን ትንሳኤ በረከት ያሳትፈን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም :
አስተያየት ይለጥፉ