ማክሰኞ 5 ኦገስት 2014

ፍልሰታ



እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!



ፍልሰታ  የሚለው ቃል  ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።
ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ በእረፍተ ሞት ከሞተች በኋላ  መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ነሐሴ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን እንዲጾም  ዋርያዊት የሆነች ቤተ ክርስቲያናችን  በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
እመቤታችን ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲያሴሩ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰዱቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክት /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት ጥር ነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳዩትም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች» በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች።
የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።
ንጉስ ሰሎሞን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ቁጥር ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ ...ዉበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።
እግዚአብሔር ከእመቤታችን ትንሳኤ በረከት ያሳትፈን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ቅዳሜ 19 ኤፕሪል 2014

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን


እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !

"
ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤" ሮሜ.6፤5

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረው በቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ ኋላም በየጊዜው በተነሡት ተከታዮቹ ምእመናን ነው፡፡
ሲወርድ ሲወራረድ ከዚህ በደረሰው ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንይህንን አብይ በዓል በዘመናት ስታከበር ኖራለች አሁንም እያከበረች ትገኛለች፡፡
መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«
ትንሣኤ» ማለት መነሣትን፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
 «
ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም አምስት ክፍል አለው፡፡
ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡
«
ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡
መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«
ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡
ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡
ሦስተኛው «ትንሣኤ» የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡  አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡
ምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ እንደተናገው ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


comment