ሐሙስ 2 ሜይ 2013

ጸሎተ ሀሙስ



·         ‹‹ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነውማቴ. 2626
·         ‹‹ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበት ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ እርሱም፦ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥በኋላ ግን ታስተውላለህ አለው።ጴጥሮስም፦የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም፦ ካላጠብሁህ፥ከእኔ ጋር እድል የለህም ብሎ መለሰለት። ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው። ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ...ግን ሁላችሁም አይደላችሁም አለው። አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ፦ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለ።
እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።እንግዲህ እኔ መምህርና ጌታ ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።" ዮሐ 13:5-15

ምንም አስተያየቶች የሉም :

አስተያየት ይለጥፉ

comment