ረቡዕ 1 ሜይ 2013

ሰሙነ ህማማት፤ረቡዕ



1-      አይሁድ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተማከሩበት ቀን ነው በዚህም ምክንያት ‹‹ምክረ አይሁድ የመልካም መግዣ ቀንና የእንባ ቀን ይባላል፡፡ ምክረ አይሁድ መባሉ አይሁድና ሊቃነ ካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር መጨረሳቸውን የመልካም መግዣ ቀን መባሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶ ከስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ ማርያም እንተ እፍረት /ባለሽቱዋ ማርያም/ ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ይዛ በጸጉሩ ላይ በማፍሰሷ የመልካም መግዣ ቀን ተብሏል፡፡ የእንባ ቀንም መባሉ ማርያም እንተ እፍረት በእንባዋ እግሩን በማጠቧ ነው፡፡
2-     የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ነው ሆኖም ዕለቱ በሰሙነ ህማመት እለት በመዋሉ የንግስ በዓሉ ወደፊት በአንድ ሳምንት ተላልፎ  በዳግም ትንሳኤ ይከበራል፡፡



ምንም አስተያየቶች የሉም :

አስተያየት ይለጥፉ

comment